የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያዩ የዳታ ሴንተር እቃዎች ፣ ሶፍትዌሮች አቅርቦት እና ገጠማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር EEP/ST/NCB/29/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያዩ የዳታ ሴንተር እቃዎች ፣ ሶፍትዌሮች አቅርቦት እና ገጠማ ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በግዥ ኤጀንሲው ድህረ ገጽ (eGP) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የግዥውን አይነት በመግለጽ፣ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን የዳታ ሴንተር እቃዎች ፣ ሶፍትዌሮች አቅርቦት እና ገጠማ ግዥ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/29/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
No |
Description |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ሎት-1
|
Servers |
2,900,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር)
|
ሀምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
|
ሀምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
|
|
Production switches |
||||
|
SAN storage |
||||
|
SAN Switches |
||||
|
Virtual management and Hyper-V |
||||
|
ሎት-2 |
Tape Library |
425,000.00 (አራት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ብር) |
||
|
All-In-One Backup Solution |
||||
|
ሎት-3 |
Supply of Servers With License |
200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) |
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ።
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
