Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ አ/አ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
  • Address ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-91-14-94-85
  • Websitehttps://etsugar.com/esig/
  • Deadline24 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security30000.00
  • opening date2025-07-25 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent , Construction Vehicle

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ጥቅል 1 ኤክስካቫተር ኪራይ አገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ አ/አ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት


 

ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ አግጨ/003/ኦኩስፋ-2/2017 ዓ.ም

 

  1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ጥቅል 1 ኤክስካቫተር ኪራይ አገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀን የባንክ ዋስትና /BID BOND/ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር /supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛው ቀን ይከፈታል። የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት፤ ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ፡-
    1. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ፡

ስልክ ቁጥር፡ +251-11-55-79 684 /09-91-14-94-85 ወይም 09-38–30-91-60

አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ

  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል 1 የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሠከረለት የ90 ቀን ሲፒኦ (CPO) ወይም በቅድመ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /BID BOND/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የተጠቀሱት አገልግሎት የሚሰጠው ደቡብ ኦሞ ዞን በኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡
  3. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው፡፡
  5.  ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ Tel. 09 40 20 94 64 /09 45 00 21 06 ሀይል ውሃ

አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ Tel. 09-91-14-94-85/09-38–30-91-60 አዲስ አበባ

 

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ አ/አ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

 

Save Tender