የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ እስፔር ፓርት፤ የተለያዩ የድንጋይ ወፍጮ አክሰሰሪዎች እና የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡- (0018/2017)
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ እስፔር ፓርት፤ የተለያዩ የድንጋይ ወፍጮ አክሰሰሪዎች እና የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው የጨረታ መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ለሚያወጡ እቃዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30-6፡00 ሰዓት እና ከሠዓት በኋላ ከ7:30-11፡00 ሰዓት፤ ቅዳሜ ከ2፡30-6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በጉምሩከ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከቀን 01/11/2017 እስከ 08/11/2017 ዓ.ም 3፡45 ሰዓት ድረስ አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመምጣትና እና ቁሽመጋን ቀበሌ በመሄድ እቃዎቹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በቀን 08/11/2017 ዓ.ም በ3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት በ4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያሲያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ተጫራቾች ደግሞ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ከፍያ ከፈፀሙ በ05 ቀናት ውስጥ እቃዎቹን ተረከበው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 7 እና 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና እቃዎቹን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ እቃዎቹ በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባሉ፡፡
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ፡- 057-4-48-37-14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የአሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
