Tender Detail

Tender Details

  • Company AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.)
  • Address ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116 637485
  • Websitehttps://africainsurancesc.com/
  • Deadline12 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security20.00
  • opening date2025-07-12 00:00:00
  • Categories

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭት እና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶበት ለደንበኛው የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከበውን 58.5 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ (ዳፕ) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭት እና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶበት ለደንበኛው የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከበውን 58.5 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ (ዳፕ) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. የአፈር ማዳበሪያውን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ሐምሌ 04 ቀን 2017 ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ ንብረቱን ቀጥሎ በተጠቀሱት አድራሻዎች በስራ ሰዓት ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
    1. አፍሪካ ኢንሹራንስ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ቦታ፣ ቃሊቲ ኖክ ማደያ በሚድሮክ ተርሚናል ወደ ውስጥ 1.5 ኪሜ ገባ ብሎ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ቅጥር ግቢ ውስጥ፤
  2. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀው እና የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22 ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አትላስ መብራት በሚወስደው መንገድ NB ቢዝነስ ሴንተር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 እስከ ሐምሌ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።
  3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሐምሌ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 22 ቺቺንያ ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አትላስ መብራት በሚወስደው መንገድ NB ቢዝነስ ሴንተር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የመነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይህን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል። ተጫራቹ በጨረታው ከተሸነፈ በማስያዣ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ የሚጫረቱበት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ስም ከፍለው እንዲወስዱ ይደረጋል። ግዥውን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የማይፈቀድ መሆኑን እየገለጽን ይህ ካልሆነ ግን አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (C.P.O) በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።
  7. ጨረታው ሐምሌ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ቦሌ አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና መ/ቤት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።
  8. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ማዳበሪያ / ንብረት ሙሉ ክፍያ 15% VAT ጨምሮ በ 7 የስራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል። ሙሉ ክፍያ ፈጽመው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለአስር ተከታታይ ቀናት በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በ 10 ቀናት ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልከ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።
  9. ለጨረታ በቀረበው ንብረት ላይ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ፣ ግብርና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚሸፈን ይሆናል።
  10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-21-89-95፣ 011-6-18-08-43 በመደወል ወይንም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መረዳት ይቻላል።
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ከእንደራስ ናሽናል ጋር በመተባበር

 

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)

 

Save Tender