Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
  • Address ኮተቤ ብረታ ብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-42-95
  • Websitehttps://www.eep.com.et/?lang=am
  • Deadline22 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-22 00:00:00
  • Categories

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር የሠራተኞች ክበብ ለክበቡ አገልግሎት ግብዓት የሚውሉ በሎት የተከፋፈሉ የአትክልት፤ ጥራጥሬ፣ ቅመማ ቅመም፣ ስጋ፣ ወተት እና የወተት ውጤቶች! የታሸጉ ምግቦች ፣ እንቁላል፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች እና የታሸገ ውሀ አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማጫረት ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር የሠራተኞች ክበብ ለክበቡ አገልግሎት ግብዓት የሚውሉ በሎት የተከፋፈሉ የአትክልት፤ ጥራጥሬ፣ ቅመማ ቅመም፣ ስጋ፣ ወተት እና የወተት ውጤቶች! የታሸጉ ምግቦች ፣ እንቁላል፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች እና የታሸገ ውሀ አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማጫረት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታ ማስታወቂያው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ሎቶች የተዘረዘሩትን የምግብ ግብአቶች ለመጫረት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
  4. የቫት/ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑ
  5. ተወዳዳሪዎች ስለሚያቀርቡት በሎት የተከፋፈለ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ሙሉ ዝርዝር ከሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው መግለፅ ያለባቸው ሲሆን ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተወዳዳሪዎች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀን ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት የሰራተኞች ክበብ ካሸር ቢሮ ከሚገኘው የግዥ ባለሙያ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ።
  7. ተወዳዳሪዎች የምታቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ ይደረጋል።
  8. የጨረታ ማስታወቂያው በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 የሚከፈት ሲሆን አቅራቢዎች በሰዓቱ አለመገኘታቸው የማወዳደር ሂደቱን እያስተጓጉለውም።
  9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት (አቅራቢ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት በኋላ ከ1 እስከ 5 ቀናት ውስጥ ተወዳዳሪዎች ግብአት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. አትክልት አሸናፊ ተወዳዳሪዎችም ሆነ ጨረታ ማስታወቂያ ያወጣው ድርጀት ከ2 ወር በፊት ዋጋ ማሻሻያ /ማቅረብ አይችሉም።
  11. ክበቡ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የጨረታ ማስታወቂያውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት

ለበለጠ መረጃ 0944743743 /0911874651 ይደውሉ።

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

 

Save Tender