በኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን የደብረ ታቦር እና ኮሶበር አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ቢሮዎች አጥር በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ውስን የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ-ባሪ/ግብጨ/010/2017
በኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን የደብረ ታቦር እና ኮሶበር አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ቢሮዎች አጥር በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና BC/GC-5 እና ከዛ በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሠነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በባሕር ዳር ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ባሕር ዳር ቀበሌ 05 (ድብ አንበሳ ሆቴል ጎን) 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በተ.ቁ 2 በተገለጸው አድራሻ ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0583206999/0583206775 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባሕር ዳር ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
