Tender Detail

Tender Details

  • Company Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)
  • Address ዋና መ/ቤት የድሮ መርከብ ሕንፃ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አጠገብ ያለው ሕንፃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115539535
  • Websitehttps://www.fhc.gov.et/en#New
  • Deadline22 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-22 00:00:00
  • Categories Construction and Water Works , Road And Bridge Construction

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአስፋልት ኮንክሪት እና የፋዎንቴን ስራ ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር FHC/NCB/ PW/22/10/2017 ደረጃ 4 እና ከዛ በላይ የሆኑ የመንገድ ስራ ተቋራጭ እና ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ (RC-4, GC -4 & Above) ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

FHC/NCB/PW/22/10/2017

 

  1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአስፋልት ኮንክሪት እና የፋዎንቴን ስራ ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር FHC/NCB/ PW/22/10/2017 ደረጃ 4 እና ከዛ በላይ የሆኑ የመንገድ ስራ ተቋራጭ እና ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ (RC-4, GC -4 & Above) ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
  2. ኮርፖሬሽኑ ለአስፋልት ኮንክሪት እና የፋዎንቴን ስራ ግንባታ ግዥ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
  3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኼንኑ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ መሠረት ሲሆን ደረጃ 4 እና ከዛ በላይ የሆኑ የመንገድ ስራ ተቋራጭ እና ጠቅላላ የስራ ተቋራጭ 2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
  4. የተሟላ የጨረታ ሰነድ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ወይም ሀምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺ ብር) ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሀምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

በስልከ ቁጥር 011-855-30-35 ወይም

011-553-95-35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender