Tender Detail

Tender Details

  • Company የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)
  • Address ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 896 06 33
  • Websitehttps://dcde.gov.et/#
  • Deadline16 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-16 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለሀዋሳ ከተማና ዙሪያው ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ፒክአፕ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCDE 028/2017

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለሀዋሳ ከተማና ዙሪያው ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ፒክአፕ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ፣ በዘርፉ የታደስ የንግድ ፈቃድ፤ የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በፊት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ከሰኔ 25 ቀን 2017 እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።

 

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23

አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ

 

Save Tender