Tender Detail

Tender Details

  • Company ሳህሌ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Address ቦሌ ኬኬር : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-35-98-83-02
  • Website
  • Deadline17 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-17 00:00:00
  • Categories Furniture , Materials

ድርጅታችን ሳህሌ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በድርጅቱ መጋዘኖች የሚገኙ አዳዲስና መጠነኛ ጉዳት ያለባቸው የተለያዩ የቤትና የቢሮ ፈርኒቸርና ሌሎች የአዳራሽና የላይብረሪ መገልገያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ሳህሌ ኃ/የተ/የግ/ማህበር


 

የቤትና የቢሮ ፈርኒቸር፣ የአዳራሽና የጨረታ የላይብረሪ መገልገያዎችና መጋረጃ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ድርጅታችን ሳህሌ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በድርጅቱ መጋዘኖች የሚገኙ አዳዲስና መጠነኛ ጉዳት ያለባቸው የተለያዩ የቤትና የቢሮ ፈርኒቸርና ሌሎች የአዳራሽና የላይብረሪ መገልገያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤ በዚህ መሰረት ማንኛውም ተጫራች፡

  • ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-8፡00 ሰዓት ቦሌ ኬኬር 2ኛ ወለል ላይ ከሚገኘው የድርጅታችን ቢሮ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ዋጋ የሚሞላበትን የጨረታ ዶክሜንት መግዛት ይችላል፤
  • በመጋዘን የሚገኙ ዕቃዎችን ማየት የሚፈልግ የጨረታ ዶክመንት ግዢ የፈፀመ ተጫራች ዕቃዎቹን ከጨረታው መክፈቻ አንድ ቀን ቀደም ብሎ እስካለው ቀን ድረስ በድርጅቱ ማሳያ ወይም መጋዘን ተገኝቶ መመልከት ይችላል፤
  • ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤
  • ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ዶክመንት ላይ ብቻ በመሙላት ማህተምና የህጋዊ ወኪላቸውን ፊርማ በማሳረፍ በሰም በታሸገ ኢንቮሎፕ ማቅረብ አለባቸው፤
  • የጨረታ ዋጋውን አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ለጨረታ ማስከበርያ ማስያዝ አለበት፤
  • ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ዶክመንት የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላል፤
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ የጨረታ መከፈቻው ቀን በዓል ከሆነ ወይም የሥራ ቀን የማይሆን ከሆነ በቀጣይ ባለ የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፤
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ በፅሁፍ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የጨረታ ዋጋ ሙሉ ለሙሉ ከፍሎ አሸናፊ የሆነበትን ዕቃዎች ከድርጅቱ መጋዘን ማንሳት አለበት፤
  • በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎቹን ሙሉ ለሙሉ የማያነሳ ከሆነ ግን ያስያዘው የጨረታ ማስከበርያ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ወደ ድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሽናፊነቱ ይሰረዛል፤

ሳህሌ ኃ/የተ/የግ ማህበር፣ ቦሌ ኬኬር፣ ስልክ ቁጥር 09-35-98-83-02

 

ሳህሌ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 

Save Tender