በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ እቃዎችንና ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 17-2017
በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ እቃዎችንና ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በተሽከርካሪዎች ጨረታ እድሜው ከ18 በላይ የሆነ ከተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሌሎች በተ/ቁጥር 1 የተገለጹ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ (መታወቂያ) ኮፒ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፤
- ከላይ በተ/ቁ 1 የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መሰፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም/አያስፈልግም።
- የሃራጅ ጨረታው ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ይካሄዳል፡፡
- ተጫራቾች ለሃራጅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች እስከ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፤ ገቢ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ግቢ ያደረጉበትን የባንከ አድቫይስ ገቢ ሂሳቦች አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 207 እስከ ጨረታው ቀን ሰኔ 26 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ድረስ ማስያዝ አለባቸው!
- በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (15%) የሚጨመር ይሆናል፤
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ 5 /በአምስት/ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ማንሳት ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፤
- በጨረታ ከሚሸጡ ተሽከርካሪ ስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል ማናቸውም ወጪ መ/ቤቱ አይሸፍንም፣
- በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፤
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልከ ቁጥር 058-320-74-18/058-320- 75-69 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻ፡- በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁስት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
