የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል የፕሪንተር ቀለም እና የፎቶ ኮፒ ቀለም ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር DCE/ ST/117/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል የፕሪንተር ቀለም እና የፎቶ ኮፒ ቀለም ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
የዕቃው አይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
የፕሪንተር ቀለም እና የፎቶ ኮፒ ቀለም |
ለዋና መ/ቤት |
DCE/ST/117/2025 |
ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም 4:15 ሰዓት |
ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም 4:30 ሰዓት |
20,000,00 |
ስለሆነም :
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅረቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ... ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠና የተረጋገጠ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታድየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 440-3434
ማዞሪያ 011 442-2270/71/72
E-mail አድራሻ info@dce.et.com
የድረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
