መ/ቤታችን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በጉለሌ የሚገኙ ቢሮዎችን ለማሳደስ በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)
ለቢሮ ዕድሳት ስራ /Office Renovation Works/ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ስተአ/002/2025
የአገልግሎት መ/ቤታችን በጉለሌ የሚገኙ ቢሮዎችን ለማሳደስ በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም የመንግሥት ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ፤ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ በጨረታ ለመሳተፍ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና በግንባታ ዘርፍ ስራ GC 4 እና GC 5 የሆኑ ተቋራጮችን በብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ውል በመግባት ስራውን ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ሚካኤል ከሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና መ/ቤት የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመምጣትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት፤ ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ስራ ቀናት አይደሉም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጥቅል ዋጋ 2 /ሁለት/ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በ F.D.R.E Refugees and Returnees Service ስም በተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ-ሁኔታ ላይ ያልተገደበ የባንከ ዋስትና ደብዳቤ፣ የዕድሳቱን ዋጋ፣ በቀረበው ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ መሰረት የቴክኒክ ሰነድ እና እንዲሁም በጨረታ ሠነዱ የተዘረዘሩትን የብቃትና የልምድ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚያያዙ ማስረጃዎች በሙሉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላበቃላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሠነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 10ኛው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ከታች በተመለከተው አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የሰራተኞች ክበብ ምድር ቤት ይከፈታል። ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው ከማምጣታቸው በፊት አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 (አራት) ዕንቁላል ፋብሪካ የሚገኘውን እና የሚታደሰውን ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት መመልከት እና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ከአራት ዓመት ወዲህ ቢያንስ ሁለትና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ስለመስራታቸው ከአሰሪዎቻቸው የመልካም አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ በኋላ የቅድመ ክፍያ እንዲከፈላቸው የሚጠይቁ ከሆነ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ውል በሚፈርምበት ወቅት የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስከበሪያ /Performance bond/ የጨረታውን አጠቃላይ ዋጋ 10% በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/F.D.R.E Refugees and Returnees Service/ ስም በተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ-ሁኔታ ላይ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የዕድሳት ስራው በሁለት ሎቶች (Lots) ተከፋፍሎ ለጨረታ የቀረበ ሲሆን አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በመረጠው አንድ ሎት ብቻ ነው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ፈርመው ወደ ስራ ከገቡበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 60 (ስልሳ) ቀናት ውስጥ ስራውን አጠናቀው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
የስልክ ቁጥር፡- 09-97-23-66-31
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
