የራያ ዋከና ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ያገለገሉ ሁለት (2) ጃንደር ኮምፓይነሮችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የራያ ዋከና ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ሃላፊነቱ የተወሰነ
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የራያ ዋከና ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ያገለገሉ ሁለት (2) ጃንደር ኮምፓይነሮችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳሰብን፡-የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኮምፓይነሮቹ በሚገኙበት አድራሻ በአካል በመገኘት መመልከት የሚችል ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሚገዙት ኮምፓይነር ከጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ (5%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለ 30 ቀናት የሚቆይ ዋስትና አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ መግዣ የሚውል 500 የማይመለስ ብር (አምስት መቶ ብር) ለዩኒየኑ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የተሳሳተ መረጃ ማቅረባቸው ከተረጋገጠ ዩኒየኑ ከውድድሩ ማሰናበት ይችላል።
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉበትን ቀን አንስተው በአምስት (5) ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን ከጨረሱ በኋላ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
- የሰነድ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን ከ7/10/17 እስከ 27/10/17 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ27/10/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዛው እለት በ 4፡30 የዩኒየኑ ቦርድ አባላት እና ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙት ሰነድ ውስጥ ስም እና ሙሉ አድራሻ በግልጽ በማስቀመጥ ፊርማውንና ማህተሙን መምታት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ በሚቀርበው ሰነድ ውስጥ ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው አድርገው መስራት አለባቸው /ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹ/ ተወካዩ ፊርማ ከፊት ለፊቱ መኖር አለበት፡፡ እንዲሁም ደግሞ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን እና ሰነዱን በአንድ ፖስታ አሽገው በማህተም በማረጋገጥ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ላይ የሚሳተፍ ተጫራች አንድ ወይም ሁለት ኮምፓይነሮች ላይ መጫረት ይችላል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የንብረት ስም ዝውውር በሚያደርግበት ሰዓት ወጪውን በራሱ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ኮምፓይነሩን ሲረከብ ከነሙሉ ዕቃው ይሆናል፡፡
- የምዝገባ ሰዓት ጠዋት 2፡30-6፡30 ከሰዓት ከ7፡30-11፡00 የስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
አድራሻ፡- ኦሮሚያ ክልል ፣ ም/ዕ አርሲ ዞን ፣ ዶዶላ ከተማ 02 ቀበሌ ፣ ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ጎን ይገኛል፡፡
ራያ ዋከና የገበሬዎች ኅ/ሥ/ዩኒየን ኃላ/የተ
