የሉሜ ወረዳ ፍ/ቤት የፍ/ብሔር ችሎት ቡድን በአፈፃፀም ክርክር በተመለከተ ፍ/ቤቱ በ9/9/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የዶሮ እርባታ ንብረትነቱ የፍርድ ባለዕዳ የሆነው በቢዮ ቢሲቄ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውን እንዲሸጥ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
በሉሜ ወረዳ ፍ/ቤት የፍ/ብሔር ችሎት ቡድን
የዶሮ እርባታ ቤት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የፍርድ ባለመብት ቢ እና እና ዋይ ዋይ ፖሊተሪ ፋርም የግል ማህበር እና የፍርድ ባለዕዳ አቶ መንግስቱ የሺጥላ መካከል ያለው የአፈፃፀም ክርክር በተመለከተ ፍ/ቤቱ በ9/9/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የዶሮ እርባታ ንብረትነቱ የፍርድ ባለዕዳ የሆነው በቢዮ ቢሲቄ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው የጨረታ መነሻ 103, 862, 467.62 (አንድ መቶ ሦስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ሰባት ብር ከ62/100) እንዲሸጥ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ እናንተም ይህንን አውቃችሁ የጨረታ ንብረት በሚገኝበት ቦታ በመገኘት በ13/11/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት የጨረታ መነሻ ብር ¼ ኛውን በሲፒኦ በማስያዝ ግልፅ በሆነ ጨረታ በጨረታ ቦታ ቀርባችሁ በጨረታ ላይ እንድትሳተፉ እና እንድትገዙ የሉሜ ወረዳ ፍ/ቤት አሳውቀዋል፡፡
በሉሜ ወረዳ ፍ/ቤት የፍ/ብሔር ችሎት ቡድን
