Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline08 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-08 00:00:00
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኦክስጅን, የካርቦን ዳይኦክሳይድ እና አሴቲሊን ጋዝ ሙሌት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በድጋሚ አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T542

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኦክስጅን, የካርቦን ዳይኦክሳይድ እና አሴቲሊን ጋዝ ሙሌት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በድጋሚ አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሰው አገልግሎት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ TIN (የግብር መለያ ቁጥር) ያለውና በዘርፉ እየሰራ ያለ ማንኛውም ተቋም በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T542 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጂውን (Deposit Ship Copy) ፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ባንክ ጋራንቲ (unconditional bank guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ከተለየ በኃላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።

ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እሰከ ሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ፕሮኪውርመንት እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ክፍል

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

በስልክ ቁጥር 011 517 8025/4028

ኢ-ሜይል: KidistTa@ethiopianairlines.com

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

 

Save Tender