Tender Detail

Tender Details

  • Company የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አሶሳ ፡ ቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 057-44-83-714
  • Website
  • Deadline23 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-23 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶላ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች በሁለተኛ ዙር ሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

ለሁለተኛ ዙር የወጣ የሀራጅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- (05/2017)

 

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶላ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች በሁለተኛ ዙር ሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ማንኛውም የድርጅት ተወካይ ወይም ግለሰብ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ጨረታውን መካፈል/መሳተፍ ይችላል፡፡
  2. በሀራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ተጫራቹ መግዛት ለሚፈልገው ሞተር ሳይክል ለእያንዳንዱ በተናጠል 4,000 ብር ለጨረታ ዋስትና (CPO) በጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ከቀን 10/10/2017 እስከ 16/10/2017 ዓ.ም ድረስ አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት ተሽከርካሪዎቹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በዚያው እለት በ4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው የሚጀመር ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች ጨረታው ከመጀመሩ በፊት አስቀድመው መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታው ማካሄጃ ቦታ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ነው፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያሲያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ተጫራቾች ደግሞ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ክፍያ ከፈፀሙ በ05 ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ተረከበው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ከላይ በተራ ቁጥር 7 እና 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ተሽከርካሪዎቹን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪዎቹ በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባሉ፡፡
  10. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- 057-4-48-37-14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአሶሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender