Tender Detail

Tender Details

  • Company ንጋት የሜካኒካል ምህንድስና አክሲዮን ማኀበር (ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ፋብሪካ)
  • Address የካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 448/1 ኮተቤ መብራት ኃይል ዋናው መ/ቤት ፊት ለፊት, Phone: 0116463041
  • Website
  • Deadline27 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-27 00:00:00
  • Categories Vehicle

ንጋት የሜካኒካል ምህንድስና አ.ማ ወይም የቀድሞ (ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ፋብሪካ) ሲገለገልባቸው የነበሩትን ሊፋን አውቶሞቢል እና ቶዮታ ላንድክሩዘር የሆኑትን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ንጋት የሜካኒካል ምህንድስና አክሲዮን ማኀበር (ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ፋብሪካ)


 

በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ንጋት የሜካኒካል ምህንድስና አ.ማ ወይም የቀድሞ (ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ፋብሪካ) ሲገለገልባቸው የነበሩትን ሊፋን አውቶሞቢል እና ቶዮታ ላንድክሩዘር የሆኑትን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  • ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት ቦታ፡- ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ፋብሪካ
  • የተሽከርካሪዎቹን ዓይነትና ሞዴል እንዲሁም ዝርዝር መግለጫዎችን ከጨረታ ሰነድ ላይ መመልከት ይቻላል።

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎቹን ጨረታ ማስረከቢያ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ ትክክለኛነቱ በተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መወዳደር ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ለተሽከርካሪዎቹ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የተሽከርካሪውን ሁኔታ መመልከት የሚችሉት የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ብቻ ነው።
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (ከሰኔ 9/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም) በሥራ ሰዓት ተሽከርካሪዎቹን ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት በፊት በሥራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት ድርጅቱ ድረስ በግንባር ቀርበው የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ጨረታውን ካሸነፈ በጠቅላላም ሆነ በተናጠል መግዛት ይችላሉ።
  6. ጨረታውን ያላሸነፈ ተጫራች ያስያዘው ገንዘብ ወይም ጋራንቲ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ተመላሽ ይሆናል።
  7. ተሽከርካሪውን በገዥው ስም እንዲዛወር ድርጅቱ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  8. ለስም ማዘዋወሪያ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ወጪ ገዥው ይሸፍናል ወይም ይከፍላል።
  9. በተሽከርካሪው ሽያጭ ላይ የሚጠየቀውን ተጨማሪ እሴት ታክስ ገዥ ይሸፍናል።
  10. ጨረታው በማስታወቂያ በወጣ በ10ኛው ቀን ስኔ 20/2017ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ እለት ጠዋት በ4፡30 ሰዓት ላይ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  11. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- ንጋት የሜካኒካል ምህንድስና አ.ማ (ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ፋብሪካ) የካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 448/1 ኮተቤ መብራት ኃይል ዋናው መ/ቤት ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር ፡- 0116463041፤ 0938003919፤ 0911226989

 

Save Tender