Tender Detail

Tender Details

  • Company ETHIOPIAN LOTTERY SERVICE (የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-126-78-16
  • Website
  • Deadline02 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-02 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በዋናው መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው አስፋልት በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ አሁን ላይ የተጎዳና የተቆፋፈረ በመሆኑ በአዲስ መልክ የአስፋልት ስራውን ለማሰራት ደረጃቸው GC/BC-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የመንገድ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ETHIOPIAN LOTTERY SERVICE (የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ/007/2017

 

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በዋናው መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው አስፋልት በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ አሁን ላይ የተጎዳና የተቆፋፈረ በመሆኑ በአዲስ መልክ የአስፋልት ስራውን ለማሰራት ደረጃቸው GC/BC-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የመንገድ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ስራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈልና በመግዛት መወዳደር ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማሲያዝ ያለባቸው ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /Irrevocable or Unconditional Bank Guarantee from Recognized Bank of Ethiopia/ ማሲያዝ አለባቸው።

ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፁትን የቴክኒካል ሰነዶችን የያዘ አንድ ዋናና አንድ ቅጂ ለየብቻው፣ የፋይናንሻል ሰነድ የያዘ አንድ ዋናና አንድ ቅጂ ለየብቻው እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለብቻው በፖስታ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ እስከ ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው።

ጨረታው ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-126-78-16 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት

 

Save Tender