ፍሬገነት ኪዳን ለሕፃናት ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም ያለውን የአንድ ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴ በመስኩ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡
ፍሬገነት ኪዳን ለሕፃናት ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት
የኦዲት ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍሬገነት ኪዳን ለሕፃናት ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዋጅ ቁጥር 1113/2011 የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ በመዝገብ ቁጥር 0821 ዳግም ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ እየሠራ ያለ ድርጅት ነው፡፡ ስለሆነም ድርጅቱ ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም ያለውን የአንድ ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴ በመስኩ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የመስኩ ባለሙያ ድርጅቶች፡- 1ኛ/ የሙያ ፈቃድ ሠርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ፣ 2ኛ/ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ማረጋገጫ ፎቶ ኮፒ ፣ 3ኛ/ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማረጋገጫ ፎቶ ኮፒ ፣ 4ኛ/ ከፌዴራል ዋና መ/ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ፣ 5ኛ ሥራውን የሚጀምሩበትና የሚያስረከቡበትን ጊዜ ገደብ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ሰነዶቻቸውን በማሟላት ቡልጋሪያ ማዞሪያ ከመብራቱ ከፍ ብሎ ከብርሃን ሙዚየም ፊት ለፊት ባለው አዲስ አስፋልት በማይ‐ድሪም አፓርትመንት ገባ ብሎ ቢ-ሜዳ ኮንዶሚኒየም አጠገብ በፍሬገነት ኪዳን ለሕፃናት ት/ቤት በአካል በመገኘት እንድታቀርቡ እንጋብዛለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- የስልክ ቁጥር፡- 09 11 91 05 90/09 13 63 59 02
ፍሬገነት ኪዳን ለሕፃናት
