Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ
  • Address ቢሾፍቱ/ደብረዘይት ከተማ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114 33 84 03
  • Website
  • Deadline30 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-30 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent

የኢፌዲሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በጨረታ ቁጥር 01/2018 ለሠራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሠጡ  አውቶቡሶችን : ኃይሩፎችንና ዶልፈን ተሽከርካሪዎችን ለ2018 የበጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት መከራየት ይፈልጋል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢፌዲሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በጨረታ ቁጥር 01/2018 ለሠራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሠጡ  አውቶቡሶችን : ኃይሩፎችንና ዶልፈን ተሽከርካሪዎችን ለ2018 የበጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መመሪያ እና ግዴታዎች በማሟላት መሃተፍ ይችላሉ፡፡

አጠቃላይ መመሪያ

  1. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ በዘርፉ የተሠማሩ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የታደሠ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ሆነው የተጠቀሱትን ሠነዶች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብና ዋናውን ቅጂ ሲጠየቁ ለኮሚቴው ማሣየት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ያካሄዱ ለመሆናቸው የምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ኢንሹራንስ የገቡበትንና የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ሊብሬ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ትክክለኛ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስማቸውንና ፈርማቸውን በጨረታ ሠነዱ ላይ በግልፅ ማስፈር አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ በፖስታው ላይ የተወዳደሩበትን የግልጽ ጨረታ ቁጥር ወይም የጨረታውን አይነት ማስፈር ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ድርጅት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይፈቀድም፡፡
  5. ተጫራቾች የተሽከርካሪ አይነት፣ የመቀመጫ ወንበር ብዛት፣ የቀን ከፍያ መጠንና የሠሌዳ ቁጥር በትክክል በሠነዱ ላይ ባለው ሰነድ መሰረት ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ቀን ጀምሮ በተከታተይ ባሉት 15 የስራና የበአል ቀናቶችን ጨምሮ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሾፍቱ/ደብረዘይት ከሚገኘው ኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ዋና በር በመምጣት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ተዘግቶ ከሰዓት 7:30 ላይ ቢሾፍቱ/ደብረዘይት ከተማ በሚገኘው የኢፌዲሪ አየር ኃይል መኮንኖች ክበብ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  8. ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሠነድ እንዲሁም ማንኛውም ግልጽ ያልሆነ የተሠረዘ የተደለዘ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የስምሪት መስመር የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ/ በባንከ በተመሰከረለት የባንክ ቼከ / ሲፒአ/ ማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ሲፒኦ አሸናፊው እንደተለየ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ይደረጋል፡፡ ለአሸናፊ ተጫራቾች ውል እንደተፈረመ ተመላሽ ይደረጋል።
  10. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውል እንዳሰሩ ተሽከርካሪዎቻቸው የሚውሉት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል በሚያዘጋጀው ቦታ ብቻ ይሆናል፡፡
  11. በአንድ ተሽከርካሪ ከአንድ መስመር በላይ መጫረት አይፈቀድም፡፡
  12. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ3 ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ውሉን መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃና ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114 33 84 03 ወይም 0114 33 80 40 የውስጥ መስመር 1330/1446 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ

 

Save Tender