የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል በ2006 ዓ.ም የተቋቋመ ፕላይውድ ጣውላ አምራች ድርጅት ሲሆን ከአሁን በፊት የነበረውን አጠቃላይ መዋቅር /structure/ በአዲስ መልክ የሠራተኛ የሥራ መደብ፤ ደረጃ ደመወዝ፡ እርከን እና አጢቃላይ የፋብሪካውን መዋቅር ማስጠናት ስለሚፈልግ በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶች እንድትወዳደሩ ይጋበዛል፡፡
Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር DWP/Pu-03/84/17 ቀን 02/10/2017
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል በ2006 ዓ.ም የተቋቋመ ፕላይውድ ጣውላ አምራች ድርጅት ሲሆን ከአሁን በፊት የነበረውን አጠቃላይ መዋቅር /structure/ በአዲስ መልክ የሠራተኛ የሥራ መደብ፤ ደረጃ ደመወዝ፡ እርከን እና አጢቃላይ የፋብሪካውን መዋቅር ማስጠናት ስለሚፈልግ በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶች እንድትወዳደሩ ይጋበዛል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው።
- በትክክለኛው የስራ መስክ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም ከአሁን በፊት ከሰራባቸው ተቋማት ቢያንስ ሁለት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችል፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው፡
- የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ ፈርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
- ማንኛውም ተጫራች አሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን/ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታግድም፡፡
- የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፤ ቅዳሜ ሙሉ ቀን የድርጅቱ የሥራ ቀን ነው፡፡
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011637 58 03 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
