Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Teachers Association /EI/ /የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር/ /ኢመማ/
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251115537227
  • Websitehttps:// ethiopianteachers.org
  • Deadline07 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-07 00:00:00
  • Categories

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከደቡብ ኢትዮጵያ፤ ከሲዳማ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበራት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ መናኸርያ ክፍለ ከተማ ጉበ ቀበሌ ከአዲሱ ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስቴድየም ፊት ለፊት የሚያስገነባው የጋራ ሁለገብ G+6 ህንጻ የተለያዩ የፊኒሽንግ ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ ስራ ተቋራጭ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Teachers Association /EI/ /የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር/ /ኢመማ/


 

2. ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከደቡብ ኢትዮጵያ፤ ከሲዳማ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበራት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ መናኸርያ ክፍለ ከተማ ጉበ ቀበሌ ከአዲሱ ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስቴድየም ፊት ለፊት የሚያስገነባው የጋራ ሁለገብ G+6 ህንጻ የተለያዩ የፊኒሽንግ ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ ስራ ተቋራጭ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. በአሉሚኒዩም እስትራክቸር ግንባታ እና ተያያዥ ዘርፍ ወይም BC&GC 6 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው በዘርፉ 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለው የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን በሲዳማ ክልል መናኸርያ ክፍለ ከተማ ሚሊንየም ቀበሌ ከሜሪ ስቶፕ ክሊኒክ ገባ ብሎ አቡነ ጎርጎርዮስ አፀደ ህጻናት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ወይም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ከዳሸን ባንከ ዋና መስሪያ ቤት አለፍ ብሎ በሚገኘው ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ግቢ ከሚገኘው ከማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ በተከታታይ ስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካይ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም በማሸግና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናል ሁለት ፎቶ ኮፒ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶች እንዲሁም የኮንስትራክሽን ማህበሩ ህጋዊነት የሚገልጹ የተሟላ ሰነዶች ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም ሰነዶችን በሌላ አንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በሰም በማሸግና የማህበሩን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ ተከታታይ በስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. አሸናፊው የውል ማስከበሪያ 10% ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ለመስሪያ ቤቱ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት
  5. ጨረታው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የኢ.መ.ማ የደቡብ. ኢ/ሲዳማ/ማዕከላዊ.ኢ /ደቡብ ምዕራብ ኢትዮ መምህራን ማህበር ሀዋሳ በሚገኘው ጂ+6 ሁለገብ ህንፃ ላይ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተዘግተው 5፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር፡- +251 911480257 /924 605805

+251 911031038/936731753

+251 916368549/924652528 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር /ኢመማ/

 

Save Tender