Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሚት ቁጥር 2 የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማህበር
  • Address ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካ ጀርባ በሚገኘው ኮንዶሚኒየም ሰሚት ቁጥር 2 የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማህበር : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251937474353
  • Website
  • Deadline04 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-04 00:00:00
  • Categories Construction Works

በሰሚት ቁጥር 2 የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማህበር በሚገኘው ግቢ ለሚሰራው የፊት ለፊት አጥር ግንባታ ስራ በኮንስትራክሽን ስራ ደረጃ አምስት (5) እና ከዛ በላይ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የሰሚት ቁጥር 2 የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማህበር


 

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ሰሚት ቁጥር 2 የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማህበር 004/2017

 

በሰሚት ቁጥር 2 የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማህበር በሚገኘው ግቢ ለሚሰራው የፊት ለፊት አጥር ግንባታ ስራ በኮንስትራክሽን ስራ ደረጃ አምስት (5) እና ከዛ በላይ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ
  3. Tin No የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አለበት
  4. የመንግሥት የግብር እዳ ነፃ መሆናቸው (Tax Clearance) ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት
  5. የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ማቅረብ አለበት
  6. የሶስት አመት የኦዲት ሪፖርት ያለፉትን ሶስት አመታት ማቅረብ አለበት
  7. ስራ ተቋራጩ የሰራቸውን የስራ ልምድ እና መልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ አለበት
  8. በሳይቱ ላይ በመቅረብ የሳይት ዕይታ በፎቶ ማቅረብ አለበት
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ የሥራ ቀናት/ በማህበሩ ጽ/ቤት በማቅረብና ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ።
  10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር (21) ሃያ አንድ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል።
  11. ሳጥኑ በሃያ አንደኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በማህበሩ ጽ/ቤት በግልጽ ይከፈታል።
  12. ተጫራቾች የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነዶችን አንድ ኦርጅናል ዶክመንት እና አንድ ኮፒ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነዶችን በተናጠል በሰም በማሸግ በጠቅላላ በእናት ፖስታ በማሸግ በማህበሩ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  13. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ በማህበሩ ትክክለኛ ስም “ሰሚት ቁጥር 2 የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማህበር" በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስገባውን ዋጋ 2 ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል CPO ለብቻው በሰም በማሸግ በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ በማሸግ ማስገባት አለበት ።
  14. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው ።
  15. የጨረታ ሠነዱን የገዙበት ደረሰኝ ከቴክኒካል ዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት ።
  16. ማህበሩ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ሰሚት ፔፕሲ ፋብሪካ ጀርባ በሚገኘው ኮንዶሚኒየም ሰሚት ቁጥር 2 የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማህበር

ስልክ ቁጥር፡- +251 937-47-43-53/+251 942-86-18-18/+251 911-42-10-77

 

የሰሚት ቁጥር 2 የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማህበር

 

Save Tender