Tender Detail

Tender Details

  • Company Harari Housing Development & Government Construction Agency (የሐረሪ ቤቶች ልማት እና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
  • Address Harar, Ethiopia, Phone: 025-6671219
  • Websitehttps://hararihousingdeve@gmail.com
  • Deadline27 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-27 00:00:00
  • Categories

በጨረታ ቁጥር HHDGC/07/17 የሐረሪ ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በቅርቡ ባሰራቸው የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንፃ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ስፋት ያላቸው የንግድ ቤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ይፈልጋል።

Harari Housing Development & Government Construction Agency (የሐረሪ ቤቶች ልማት እና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በጨረታ ቁጥር HHDGC/07/17 የሐረሪ ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በቅርቡ ባሰራቸው የመምህራን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንፃ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ስፋት ያላቸው የንግድ ቤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ይፈልጋል።

  1. ኤጀንሲው ለሽያጭ ያቀረባቸውን እነዚህን የንግድ ቤቶች በጨረታ ተወዳድሮ ለማግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ቀጥሎ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በሐረሪ ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ /ሂሳብ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቹ ለሚጫረትበት የንግድ ቤት ከሚሰጠው ጠቅላላ ዋጋ 2% የሚሆነውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  3. ተጫራቹ ለሚወዳደርበት የንግድ ቤት ሞልቶ ከሚያቀርበው የመልስ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር ጨረታ ሰነዱን የገዛበት ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አብሮ አያይዞ ማቅረብ አለበት።
  4. የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው ሊሳተፍ አይችልም።
  5. የጨረታ ማቅረቢያ ሰነዱ በታሸገ ፖስታ ሆኖ በፖስታው ላይ የተጫራቹ ሙሉ ስም አድራሻና ፊርማ፤ እንዲሁም ተጫራቹ ሊገዛው የተወዳደረበት የንግድ ቤት የሚገኝበት አካባቢ (ሳይት) የሕንፃ ቁጥር፤ የሕንፃ ዓይነት የቤት ቁጥር በግልጽ መገለጽ አለበት።
  6. በተወዳደረበት የንግድ ቤት አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሚመለከተው በሐረሪ ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የቤት ማስተላለፍና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ቀርቦ የቤት ሽያጭ ውል ያልፈረመ ተጫራች ያስያዘው (CPO) ገቢ ተደርጎ ከጨረታው ይሰረዛል።
  7. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በወጣ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይዘጋል። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
  8.  ጨረታው ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በወጣ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሐረሪ ቤቶች ልማትና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይከፈታል።
  9. ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ፡- 025-6671219 / 0915-092156

 

የሐረሪ ቤቶች ልማት እና የመንግስት ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

 

Save Tender