Tender Detail

Tender Details

  • Company የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ቡታጅራ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-145-67-77
  • Website
  • Deadline11 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-11 00:00:00
  • Categories Building Construction

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ በድጋሚ የወጣው የአቱ ት/ቤት የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ ግዥ እና 2ተኛ የቡታጅራ ከተማ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 005/2017 ዓ.ም

 

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ በድጋሚ የወጣው የአቱ ት/ቤት የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ ግዥ እና 2ተኛ የቡታጅራ ከተማ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ተጫራቾች ፡-

  1. ለአቱ ትምህርት ግንባት ጨረታ መወዳደር የሚችሉት ደረጃ 9 (ዘጠኝ) የግንባታ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት ብቻ ሲሆኑ
  2. ለቡታጅራ ከተማ ለአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ግዥ ጨረታ መወዳደር የሚችሉት BC4: GCS እና ከዚያ በላይ የግንባታ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች መሆን አለባቸው፡፡
  3. በተጨማሪም ለሁለቱም የግንባታ ጨረታዎች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፤ የቲን ነምበር ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል ፤ በተጨማሪም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን ሁሉ ማቅረብ ይኖራባቸዋል ፡፡
  4. አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ጨረታ የምትወዳደሩ ድርጅቶች የሚገነባበትን ቦታ ማየት /Site visit/ ማድረግ ግዴታ ነው።
  5. ለእቱ ትምህርት ቤት ግንባታ ግዢው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በህጋዊ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተናተጠል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ለአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ግዢው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በህጋዊ ባንክ በተረጋገጠ CPO ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተናተጠል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፈርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም ኣይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎች በአንድ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማሸግ ማለትም 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል።
  9. ይህ ጨረታ አየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ31ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 04፡30 ሰዓት ላይ ቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች/ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
  10. ተጫራች /ወኪሎቻቸው/ ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም።
  11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።
  12. ይህ የጨረታ ዋጋ ለ60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል ፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የግዥ ዓይነት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቡታጅራ ከተማ አስ/ፋ/ጽ/ቤት የግ/ንብ አስተ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-145-67-77 ወደም 046-115-06-07 ደውሎ መጠየቅ ይችላል ::

 

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

ቡታጅራ

 

Save Tender