በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ግብርና መምሪያ በካሊም ፕርግራም በጀት ድጋፍ የተለያዩ የህንጻ መሣሪያ ዕቃዎችን በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የተለያዩ የህንጻ መሣሪያ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ
ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 29/2017
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ግብርና መምሪያ በካሊም ፕርግራም በጀት ድጋፍ የተለያዩ የህንጻ መሣሪያ ዕቃዎችን በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ ለመሳተፍ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቲን ቁጥር ሰርተፍኬት እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያለውና የሚያቀርብ
- ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-8
- የዕቃዎችን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ፕሮፎርማ ሞልቶ ከተፈላጊ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ጋር በታሸገ ፖስታ አሽጎ የሚያቀርብ መሆን አለበት፣
- የጨረታ ሰነድ ለኮሬ ዞን ገቢዎች ዩኒት 50 /ሃምሳ ብር ብቻ/ የማይመለስ በመክፈል ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ታትሞ ከወጣበት እስከ ሚያበቃበት ቀን ድረስ ከፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -8 መውሰድ ይቻላል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ የሚያሲዝ መሆን አለበት፣
- የጨረታ ሳጥን የሚታሸግበትና የሚከፈትበትን ቀንና ሰዓት በተመለከተ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ወደ ፊት በሚቆጠር በ16ኛ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡15 ደቂቃ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ ዕለቱ የሳምንት እረፍት ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
- የጨረታ ሳጥን በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታ ሂደትን እያስተጓጉልም፣
- የጨረታ አሸናፊ ማሸንፉ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ ለአምስት /5/ የሥራ ቀናት ለቅሬታ አቤቱታ ጊዜ ሰጥቶ ከ8ኛው ቀን እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% በመያዝ ቀርቦ ውል ካልገቡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ለመንግስት ውርስ በማድረግ አፈጻፀሙን ለክልል ግዥ ኤጀንሲ እናሳውቃለን፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ይፋ ሲሆን ያሸነፈውን ዕቃዎችን ውል ገብተው እስከ ኮሬ ዞን ፋይንንስ መምሪያ መጋዘን ድረስ ልዩ ልዩ ወጪዎችን እራሱ ችሎ ማቅረብ አለበት፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0464570452/ 0916130084
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
