Tender Detail

Tender Details


አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች (CRAWLER CRANE MACHINE: CEMENT SILO MACHINE) በሀራጅ ጨረታ፣ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች፣ Galvanized metal coil እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


 

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች፤ ተሽከርካሪ እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 46/2017

 

አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች (CRAWLER CRANE MACHINE: CEMENT SILO MACHINE) በሀራጅ ጨረታ፣ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች፣ Galvanized metal coil እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ሰኔ 05/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።

በመሆኑም

  1. በተሽከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
  2. በመንገድ ግንባታ ማሸነሪዎች ሀራጅ ጨረታ የሚሣተፉ ተጫራቾች የመንገድ ግንባታ፣ የኮንስትራክሽን፣ የማሽነሪ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል። በተጨማሪም በተ.ቁ 3 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባቸዋል።
  3. በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ከጨረታ አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

 

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነዱ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ

ቅ/ጽ/ቤት

የዕቃ ሀራጅ

እስከ 09/10/2017

10/10/2017 4፡00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

የዕቃ ግልጽ

እስከ 10/10/2017

11/10/2017 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል

የተሽከርካሪ ግልጽ

እስከ 10/10/2017

11/10/2017 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል

የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች ሀራጅ ጨረታ

እስከ 11/10/2017

12/10/2017 4፡00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

 

በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።

  1. ተጫራቾች የመንገድ ግንባታ ማሸነሪዎች፣ የተሽከርካሪውን እና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ሰኔ 05/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
  2. በዕቃና በተሸከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ወይም ተሸከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. የመንገድ ግንባታ ማሸነሪዎች ሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ማሸሪዎች ብር 100,000.00 እና የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ.ቁ 6 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት። ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን።
  4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
  5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡- አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾ  /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  6. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
  8. ከላይ በተ/ቁ 11 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  9. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ - ስልክ ቁጥር አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ፡- 011-470 - 85-03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

 

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender