በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከ/ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የመከላከያ ውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የሚውሉ አገልግሎት በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ግ/ጨ/አገ/001/2018
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከ/ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የመከላከያ ውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ እና የሚሰጡ፡-
1ኛ. ለኮሌጃችን ማ/ሰብ ለመጠጥ፣ ለምግብ ማብሰያ ፣ ለገላና ለብስ ማጠቢያ፣ ለመፀዳጃ ቤት፣ ለግንባታ እና ቋሚ አትክልቶች እንዲሁም ለተለያዩ የልማት ስራዎች አገልግሎት የሚውል ውሃ በራሱ ቦቴ ተሽከርካሪ በአከባቢው ከሚገኙ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች በአማካይ በቀን እስከ 20,000 ሊትር ውሃ ለአንድ ዓመት ውል በማሰር በኮሌጃችን ቅጥር ግቢ ማቅረብ የሚችሉ እና በመደበኛ የጨረታ ሰነዳችን ላይ በተገለፁ ዝርዝር መገምገሚያ ነጥቦች መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡
2ኛ. የተሻለ ቁመና ያለው የቀርብ ዘመን ሞዴል ና ስሪት የሆኑ 02 (ሁለት) ኮስትር እና 02 (ሁለት) ሃይሩፍ ተሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የተለያዩ የመኖረያ ቦታዎች እና ወ/ዊ ካምፖች በስራ መግቢያ ስና መውጪያ ሰዓት በተጨማሪም ኮሌጁ በየቀኑ በሚያወጣቸው የስምሪት ፕሮግራሞች መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ሚገኙ የተለያዩ መንግስታዊ የሆኑና መንግስታዊ ያልሆኑ መ/ቤቶች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የስሪት ዘመናቸው > 2018 እ.ኤ.አ የሆኑ 02 (ሁለት) ኮስትር ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የስሪት ዘመናቸው > 2018 እ.ኤ.አ የሆኑ 02 (ሁለት) ሃይሩፍ ተሸከርካሪዎች በመደበኛ የጨረታ ሰነዳችን ላይ በተገለፁ ዝርዝር መገምገሚያ ነጥቦችና የጉዞ መስመር መሰረት የትራንስፖርት አገልግሎት በተሟላ መንገድ መስጠት ከሚችሉ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራች ድርጅቶች፡- ተጫራቾች አገልግሎት ሰጪዎች አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ አሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፣ በጨረታው ለመወዳደርና ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ስራ መስክ/ዘርፍ ፈቃድ እንዲሁም በኤጀንሲው ድረ ገፅ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ግብር ስለ መክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብቻ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከወጣበበት ቀን ጀምሮ መደበኛ የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ ግልፅ ጨረታው ከግንቦት 30/09/17ዓ.ም እስከ ሰኔ 16/10/17 ዓ.ም ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ ሰኔ 16/10/17 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ላይ ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
መከላከያ ውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ እንጦጦ ቅጥር ግቢ
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከ/ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ
የመከላከያ ውጊያ ምህንድስና ኮሌጅ
