Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት
  • Address አራዳ ክ/ከተማ፤ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጎን፤ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 አዲስ አበባ, Phone: 0111264972
  • Website
  • Deadline24 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-24 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለሠራተኞች ሰርቪስ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓትና ቀን በከተማው ውስጥ ስስራ የሚሰማራ ቢያንስ 12 ሰው አና በላይ የመጫን አቅም ያለው ብዛት 4 ተሽከርካሪዎችን የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ 2016 ወዲህ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት


 

የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አአትፕግጽ ቤ/ብግጨ /7/01/2018

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለሠራተኞች ሰርቪስ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓትና ቀን በከተማው ውስጥ ለስራ የሚሰማራ ቢያንስ 12 ሰው አና በላይ የመጫን አቅም ያለው ብዛት 4 ተሽከርካሪዎችን የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ 2016 ወዲህ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክለ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ ኦንላይን የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብና የተሽከርካሪ ባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂይ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከጽ/ቤቱ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 704 ማገኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በሚገኙበት ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡15 ሰዓት 7ኛ ፎቅ በሚገኘው በጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  5. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት አራዳ ክ/ከተማ፡ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጎን፡ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ስልክ ቁ. 011 126 4972 / 011 126 5523

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት

 

Save Tender