Tender Detail

Tender Details

  • Company አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን
  • Address አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ 22 መክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ያሬድ ቶርኖ ቤት ህንፃ ላይ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 659 18 74
  • Website
  • Deadline16 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-17 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Laboratory Equipment And Chemicals , Cloth And Shoes

መስሪያ ቤታችን አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በተለያዩ መጋዘኖች ተከማችተው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶች ማለትም የላብራቶሪ ቁሳቁስ ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና የተለያዩ ደንብ ልብሶች ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ01/2017

 

መስሪያ ቤታችን አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በተለያዩ መጋዘኖች ተከማችተው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶች ማለትም የላብራቶሪ ቁሳቁስ ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና የተለያዩ ደንብ ልብሶች ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና የፋይናንስ መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራጮች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት /ምድብ በኢፌድሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (የተመዘገበበት ቀን አቅራቢነቱ ከመስኩ ጋር የሚመሳሰል የባለቤትነት የሚገልፅ) የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ መቅረብ ይኖርበታል
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ VATተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  5. ተጫራቾች በገቢዎች ሚኒስቴር በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ መረጃ /ክሊራንስ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራጮች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር / በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 በመቅረብ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ በኮሚሽኑ የስብሰባ አዳራሽ 7ተኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል ነገር ግን ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
  7. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ሰነዱን ከገዙ በኋላ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡30-11፡00 በሚገኙበት መጋዘን ማየት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በፎርማቱ መሰረት ብቻ ሞልተው በየሰነዳችሁ ኮፒ ላይ በመፈረም የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ፤ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው 4 ፖስታ በማሸግ ፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በደንብ አሽገው ፖስታው ላይ ኮፒና ዋና ሰነድ ብለው በመለየት የግዥ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
  9. የተዘረዘሩትን ንብረቶች የምትጫረቱ ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዓይነት በዝርዝር በመግለፅ የተጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሌሎች ህጋዊ ሰነዶች ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  10. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በተናጥል ወይም ሙሉ ለሙሉ መወዳደር ይቻላል።

አድራሻ፡- አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ 22 መክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ያሬድ ቶርኖ

ቤት ህንፃ ላይ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403

ስልክ ቁጥር 011 659 18 74

 

አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

 

 

Save Tender