አምቦ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን የኦሮሚያ ሕብርት ሥራ ዩንዬን በዩንዬኖችና ሕብርት ስራ ማህበራት መጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ በተወሰነው መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
አምቦ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን የኦሮሚያ ሕብርት ሥራ ዩንዬን በዩንዬኖችና ሕብርት ስራ ማህበራት መጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ በተወሰነው መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶቹም፡-
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፈቃድ ፣ ግብር ስለመክፈል የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ይህንን ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ለምን አገልግሎት እንደሚጠቀሙበት የሚያሳይ የድጋፍ ደብዳቤ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችል ፤
- ተጫራቾች ይህንን ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደር እንደማያቀርቡ አምቦ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩንዬን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ጠቅላላ የተወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5% CPO በኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ አምቦ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዬን ስም ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን፤ የጨረታው ማስከበሪያ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ሲመለስ፤ ለአሸናፊዎች ግን ሥራውን በተዋዋሉት መሠረት ሲያጠናቅቁ አፈፃፀማቸው ታይቶ እና ተረጋግጦ የሚመለስላቸው ይሆናል።
- ተጫራቾች በዩንዬኑ መጋዘን በአካል በመገኘት ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ያለበትን ሁኔታ በማየት የተዘጋጀውን ሰነድ በብር 500 ለእያንዳንዱ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ከዩንዬኑ በመግዛት የሚገዙበትን የአንድ ኩንታል ዋጋ በብር መስጠት አለባችው፡፡
- ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት ፊት ወይም ባይገኙም ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡05 ሰዓት ጠዋት በዩኒዬኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የማስጫኛ ዋጋ ለራሳቸው የሚችሉ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በአምስት ቀን ውስጥ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ በዩንዬኑ መጋዘን ውስጥ ተሰብስቦ የሚገኘውን በመለየት ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የሚረከብ ይሆናል።
- ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በመለየት በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማሕተብ ፣ ስምና ፊርማ ተደርጎበት መቅረብ አለበት፡፡
- ዩኒዬኑ በጨረታው ላይ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ 011 260 9101፣ 0112 36 33 99 ይጠቀሙ
አምቦ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
