የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት በካራቆሬ ዕቃ ግምጃ ቤት ኮተቤ እና በክልል /አ/ኤ/አ ዕቃ ግምጃ ቤቶች አገልግሎት መስጠት የማይችሉትን ስቲል ስክራፒ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥርEEU/PPM/NCB/23/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት በካራቆሬ ዕቃ ግምጃ ቤት ኮተቤ እና በክልል /አ/ኤ/አ ዕቃ ግምጃ ቤቶች አገልግሎት መስጠት የማይችሉትን ስቲል ስክራፒ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች :-
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ማስታውቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለሎት-1 – 17,553 (አስራ ሰባት ሺ አንድ መቶ ሃምሳ ሶስት) ብር 1 ለሎት-2-14,921 (አስራ አራት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ አንድ) ብር ለሎት-3-4.851 (አራት ሺ ስምንት መቶ ሃምሳ አንድ) ብር ለሎት- 4- 148,777 (አንድ መቶ አርባ ስምንት ሺ ሰባት መቶ ሰባ ሰባት) ብር ለሎት-5 – 16,561 (አስራ ስድስት ሺ አምስት መቶ ስልሳ አንድ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በእ.ኤ.አ. ፕሮጀክት ፖርትፖልዮ ማኔጅመንት ወይም EELU-PPM ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EELU/PPM/NCB/23/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ነው በመቅረብ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ፤ከሰዓት 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎች በሚገኙበት ዕቃ ግምጃ ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል፣
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ይመልከቱ፡፡
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011275503 መደወል ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
