በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የዲመካ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በዲመካ ከተማ የከንቲባ ጽ/ቤት የቢሮ ህንፃ ግንባታ ለማስገንባት በዚህ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዢ ዘዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የዲመካ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በዲመካ ከተማ የከንቲባ ጽ/ቤት የቢሮ ህንፃ ግንባታ ለማስገንባት በዚህ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዢ ዘዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
- ደረጃ አምስት ጠቅላላ ሥራ ወይም ህንፃ ሥራ ተቋራጭ እና ከዚያ በላይ የሆነ -
- በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር - በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም በክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ በኮንስትራክሽን ባለስልጣን ተመዝግቦ ለ2017 የበጀት ዓመት ከላይ በተጠቀሰው ደረጃ መሠረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው
- ለ 2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
- ለ 2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሠርተፍኬት ያለው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
- ለ 2017 የበጀት ዓመት በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታክስ ክሊራንስ ሠርተፍኬት ያለው
- በተጠቀሰው የሥራ መስከ በጠቅላላ ወይም ህንፃ ሥራ ተቋራጭነት በአቅራቢነት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ /Suppliers List Registration certificate/
- ከላይ በተገለጸው መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አመልካች የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዢ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ከፍል የማይመለስ ብር 700 /ሰባት መቶ ብር/ በመክፈልና በመውሰድ የጨረታ ሰነዱን በሚገባ ተገንዝቦ በጨረታ ሰነዱ ላይበተገለጸው መሠረት መወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሰረት በማዘጋጀት ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በማዘጋጀት አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ /ቴከኒካሉ ላይ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ/ ለዚህ ጨረታ ሥራ በዲመካ ከተማ አስተዳደርፋይናንስ ጽ/ቤት ግዢ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በሃያ ሁለተኛው /22 ኛው ቀን (የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ 2፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል። ጨረታው በዚሁ ዕለት 6.30 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የዲመካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
