Tender Detail

Tender Details

  • Deadline20 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-20 00:00:00
  • Categories Construction Works

የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት በወራቤ ሆስፒታል ውስጥ ለሚያሰራው የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ስራ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት በወራቤ ሆስፒታል ውስጥ ለሚያሰራው የፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ስራ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው G.C-5./W.C-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን

  1. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ
  2. የንግድና የሥራ ፈቃድ በጀት ዓመት የታደሰ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የኮንስትራክሽን ከተማ ልማት ሚኒስቴር የዘመኑን ምዝገባ ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ
  4. የጨረታ ዋስትና 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ ሲሆን ለስድስት ወር የጸና መሆን አለበት ከዛ በታች ከሆነ ውድቅ ይደረጋል።
  5. የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልጽ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  6. የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱ አወቃቀርንና ከዚህ በፊት የሰራቸውን ስራዎች የሚገልጽ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል ተቋራጮች ሰነዱን ከወራቤ ኮምሬንሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሺያል ዶክመንት በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጅናልና 2 ኮፒ ለየብቻ ቴክኒካል ዶክመንትን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ውስጥ ከ8፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ከፍል 302 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ እለት በ8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-

  • ተወዳዳሪው ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል።
  • ተወዳዳሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀን አይለውጠውም
  • ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0920057024/0913213696 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ

 

የወራቤ ኮምርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

 

Save Tender