የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአረንጓዴ ስፍራዎች (ገፀ ምድር) ማስዋብ አገልግሎት ግዥን በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/28/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአረንጓዴ ስፍራዎች (ገፀ ምድር) ማስዋብ አገልግሎት ግዥን በዘርፉ ከተሰማሩና ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድህረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ የጨረታ ሰነድ እንዲሸጥላቸው የጨረታ መለያ ቁጥሩን እና የገዥውን አይነት በመግለጽ፣ በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ እና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ወጪ የሆነ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች ማስታውቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን የአረንጓዴ ስፍራዎች (ገፀ ምድር) ማስዋብ አገልግሎት የቴከኒካል እና የፋይናንሽያል ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/ST/NCB/28/2017 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ/ቁ |
Description |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የአረንጓዴ ስፍራዎች (ገፀ ምድር) ማስዋብ አገልግሎት ግዥ |
100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) |
ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት |
ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ።
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
