በዴም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለዴቻ ወረዳ አስተዳደር የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተገጣጣሚ ወይንም ፈርኒቸር መግዛት ስለሚፈልግ በዘርፉ ማለትም የቤትና የቢሮ ዕቃ ወይንም ፈርኒቸር አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
- በዴም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለዴቻ ወረዳ አስተዳደር የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተገጣጣሚ ወይንም ፈርኒቸር መግዛት ስለሚፈልግ በዘርፉ ማለትም የቤትና የቢሮ ዕቃ ወይንም ፈርኒቸር አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- በዚህም መሰረት በዘርፉ ማለትም የቤትና የቢሮ ዕቃ ወይንም ፈርኒቸር አቅራቢ ድርጅት በዘርፉ ፈቃድ ያለው በ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው የተ/እ/ታ (ቫት) ምዝገባ ም/ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ም/ወረቀት እጉዲሁም በመንግስት ግዥ (ጨረታ) በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ሁሉ በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ።
- በተጨማሪ ጨረታውን የሚያሸንፍ ተጫራች ወንበሩን እስከ ቦታው በማምጣትና በመግጠም በተመረጡ ከተማዎችና በዘርፉ ባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ክፍያ የሚፈጽም መሆኑን የሚያምን እንዲሁም የወንበር ናሙና አስቀድመው ማቅረብ የሚችል ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ብቻ ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 100.00 ብር በፈደል አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከመ/ቤታችን ግዥ ኬዝ ቲም ሰነድ በመውሰድና በዝርዝሩ መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመውሰድ ከተ/እ/ታ/ቫት) ጋር በመሙላት እንዲሁም ከላይ የተዘረዘሩ የንግድ ፈቃድና ተያያዥ የመረጃ ኮፒዎችንና የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በአንድ ፖስታ በማሸግ ዋጋ የተሞላበትን ኦሪጅናል ኮፒውን የጨረታ ሰነድ በሌላ ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዕለቱ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0945927114 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
በደ/ም/ሕ/ክ/መ/ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
አውራዳ
