Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከርካሪ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች እና አክሰሰሪው (መገናኛ መሳሪያዎች) እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ለተጫራቾች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 33/2017

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከርካሪ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች እና አክሰሰሪው (መገናኛ መሳሪያዎች) እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ለተጫራቾች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕታዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በሞያሌ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት ቁጥር (1000026238521) በስልክ ደውሎ ማሳወቅና ስሊፕ በተሌግራም ቁጥር 09-12-64-12-94/ 09-48-08-48-48 በመላክ የጨረታ ሰነድ ባለበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል፡፡
  3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው የሚካሄደው በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባለበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ ወይም በቃሊቲ ጉምሩክ ጌታስ መጋዘን (መጋዘን ቁጥር 8) መመልከት አለባቸው።
  6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው በ3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዘግቶ በ4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል።
  7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ቢቀር የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒአ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት በተገለጸ በ 3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-12-64-12-94/ 09-48-08-48-48/ 09-07-25-41-94/046-4-44-15-64 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 

Save Tender