Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
  • Address ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣ ፌሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251115500417
  • Websitehttps://etsugar.com/esig/
  • Deadline19 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-19 00:00:00
  • Categories Chemicals And Reagents

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከዚህ በታች የተገለፁትን ኬሚካሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር :- LP/OT/32/SIG/2017

 

  1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ከዚህ በታች የተገለፁትን ኬሚካሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
  1. Poly Aluminum Chloride Powder (PAC) ብዛት 2,000 ኩንታል
  2. Sulfur ብዛት 400 ኩንታል
  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ/ በጨረታ መሳተፍ እንዲችል የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተራኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ሰዓት ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ

አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ጨለለቅ አልሳም ህንጻ ፊት ለፊት ፊሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220

ስልክ ቁጥር +251-11-5-51-62-71 ወይም 115-50-04-17፣

አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ

  1. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሽግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ከሰዓት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት ቼክ (CPO) ከቴክኒከ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለዘጠና (90) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
  4. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ይሆናል።
  5. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

 

Save Tender