Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ
  • Address በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አለፍ ብሎ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሻል 100 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 2 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251111265333
  • Website
  • Deadline14 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-14 00:00:00
  • Categories Chemicals And Reagents , Chemicals And Reagents , Pharmaceutical Products , Pharmaceutical Products

በአራዳ/ክ/ከ/ወ/2 የስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ በ2017 የበጀት ዓመት የተለያዩ መድሃኒቶችና የላብራቶሪ ሬጀንቶች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ስ/ከ/ጤ/ጣ/03/2017

 

በአራዳ/ክ/ከ/ወ/2 የስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ በ2017 የበጀት ዓመት የተለያዩ መድሃኒቶችና የላብራቶሪ ሬጀንቶች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-

  1. ከሚገዛው ዕቃ /አገልግሎት ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /በዌብሳይት የተመዘገቡ ተጫራቾች ከዌብሳይቱ ላይ ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ሎት ላይ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ 2% ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) በባንክ በተረጋገጠ በጤና ጣቢያው ስም ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
  5. ተቋማችን የሚገባቸውን የአገልግሎት የዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 በመክፈል በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ 3 ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፓስታ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ግዥ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ያላካተተ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ፣ ስርዝ ድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀሙ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
  8. የጨረታው ሣጥን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ አዳራሽ ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያው እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  10. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ከውል በፊት 20% /ሀያ ከመቶ/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል።
  11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ ከራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል አለፍ ብሎ ታደሰ ቸኮል ኮሜርሻል 100 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ

ስልክ ቁጥር፡- +251 11 126 53 33/ 09 11 44 12 57 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስመኝ ከበደ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender