ድርጅታችን ዕለት ደራሽ የእርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት ለትራክር እና ሬኖ ከባድ ተሽከርካሪ የሚውል የድጋፍ ዕቃዎች /ክሪክ ፣ ገመድ ፣ ካቦ ፣ ሌባ ጎማ እና ጎማ መፍቻ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ስለሚፈልግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዕ/ደ/ዕ/ት/ድ/አቅ/016/17
ድርጅታችን ዕለት ደራሽ የእርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት ለትራክር እና ሬኖ ከባድ ተሽከርካሪ የሚውል የድጋፍ ዕቃዎች /ክሪክ ፣ ገመድ ፣ ካቦ ፣ ሌባ ጎማ እና ጎማ መፍቻ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ስለሚፈልግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ።
- የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) እና ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ስለመስራቱ የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገቢዎች ሚኒስቴር የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው በመንግስት ግዥ አቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል፤
- ተጫራቾች በቀረበው የዕቃ ዝርዝርን መሠረት በማድረግ የሚወዳደርበትን ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 10 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ ነገር ግን የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተመሠከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ፤ በታሸገ ፖስታ አድርገው በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቀረበው የዕቃ ዝርዝርን መሠረት በማድረግ የሚወዳደርበትን ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 10 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በአቅ/ፋ ማ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናል ፣ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናል፣ ፋይናንሽያል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ ፣ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ከ70% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የፋይናንሽያል ሰነድ ከ30% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የቴክኒካል ግምገማ ውጤት 70/100 ወይም 51/70 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተጫራቾች ለፋይናንሻል ውድድር ግምገማ ያልፋሉ፡፡ በፋይናንሻል ግምገማ ከፍተኛ ውጤት /ዝቅተኛ ዋጋ/ ያስመዘገበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል።
- የጨረታ አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀ ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ /የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና አገልግሎት የሚውል ያሸነፈበትን ጥቅል ዋጋ ብር 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል ይፈፅማል፤
- ድርጅቱ ይህንን ጨረታ ለአሽናፊ በሚሰጥበት ጊዜ የመግዣ የነጠላ ዋጋ ሳይቀየር ብዛት በ20% ለመጨምር /ለመቀነስ መብት አለው፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፦ በስልክ ቁጥር 011 439 00 75 / 011 439 10 27 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፦ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ነው፤
የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
