Tender Detail

Tender Details

  • Company Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
  • Address ዋናው መስሪያ ቤት አራት ኪሎ አዲስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ, Phone: 0111555230
  • Websitehttps://ethbspe.org/en_US/
  • Deadline01 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-01 00:00:00
  • Categories Building Construction

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የቃሊቲ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት የማምረቻ መጋዘን ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ድርጅታችን የቃሊቲ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት የማምረቻ መጋዘን ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚንስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸሁ እንዲሁም ደረጃ GC 4 ወይም BC 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮች የጨረታ ሰነዱን በሲዲ በድርጅቱ አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት በድርጅቱ 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብና ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጨረታው 24/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ሰነድ ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

 

ስልክ ቁጥር 0111555230

ድረ-ገጽ (www.ethbspe,org)

 

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

 

Save Tender