በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በ ሰ/ሸዋ ዞን የዓ/ከ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ማለትም 1ኛ ዘመናዊ ፓውዛ ብረት 2ኛ LED ፓውዛ 3ኛ የኤሌክትሪክ እቃዎች 4ኛ ጋቢዮን 5ኛ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በ ሰ/ሸዋ ዞን የዓ/ከ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በ ሰ/ሸዋ ዞን የዓ/ከ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ማለትም 1ኛ ዘመናዊ ፓውዛ ብረት 2ኛ LED ፓውዛ 3ኛ የኤሌክትሪክ እቃዎች 4ኛ ጋቢዮን 5ኛ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በየዘርፉ ላሉት እቃዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin number/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200.000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ እቃችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከዓ/ከ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለሞሉት የእያንዳንዱ የእቃዎች አይነት የአንዱን እቃ ጠቅላላ ዋጋ በቁጥር 30000 ብር (ሰላሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው የጨረታውን አይነት በመግለጽ በፖስታው ላይ በመፃፍና የድርጅቱን ማህተም፣ ስልክ ቁጥርና ፊርማ በመፈረም ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ22/9/2017 ዓ/ም እስከ -- 6/10/2017 ዓ/ም ባሉት15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በግዥ ቢሮ ቁጥር 13 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን ማስገባት ይቻላል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን 7/10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት 4፡00 ሰዓት ላይ የከፈታል፡፡
- ለማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 10,000 (አስር ሺህ) በላይ እና ለአገልግሎት ከብር 300 በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 2 % የቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑን ማወቅ አለባችሁ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር ቁጥር 32 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 13 20 801/395 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ሙሉ እቃ ያወዳደረው ጽ/ቤት በሚፈልገው ቦታ ወይም መጋዘን ንብረት ክፍል/የማስረከብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይቀየራል፡፡ ሆኖም ግን የመክፈቻ ሰዓት አይቀየርም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ሲሞሉ ከቫት በፊት ከነቫቱ እዲሁም ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ በሌለው መልኩ መሙላት እና ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሚገዙት ሰነዶች ከሰነዱ ጋር ከቀረበው እቃ ጋር አግባብነት ያለው ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ግዥ ፈፃሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈጸሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 30% /ሰላሳ በመቶ/ መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
- ጽ/ቤቱ እንዳስፈላጊነቱ በሎት /በጥቅል/ እና በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር/ገ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር፡- 011 132 0801/395
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በ ሰ/ሸዋ ዞን የዓ/ከ/ከ/አስ/ ገንዘብ ጽ/ቤት
