Tender Detail

Tender Details

  • Company Bahir Dar University College of Medicine and Health Sciences (የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
  • Address Bahir Dar, Amhara Region, Ethiopia, Phone: 058320-9320
  • Websitehttps://www.bdu.edu.et/cmhs/
  • Deadline13 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-13 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent , Pharmaceutical Products

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት 60 ሰው እና ከዚያ በላይ የሚጭን የመኪና ኪራይ አገልግሎት እና ለታካሚዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መድኃኒቶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Bahir Dar University College of Medicine and Health Sciences (የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት 60 ሰው እና ከዚያ በላይ የሚጭን የመኪና ኪራይ አገልግሎት እና ለታካሚዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መድኃኒቶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ እና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች በስራ ዘርፉ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ የተመዘገቡ ያለማጭበርበር ቃል የሚገቡበትን ፎርም ላይ ማህተምና ፊርማ የተደረገበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን፣ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉና የግብር ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ ሆነው የሁሉንም ሠነዶች ፎቶ ኮፒ እና ኦርጅናል ከጨረታ ሠነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተራ ቁጥር 6 በተገለፀው ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከሰባታሚት ግቢ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ከፍል መግዛት ይችላሉ።
  3. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ ዋናውን እና የማይመለስ ኮፒውን በማሣየት ያለክፍያ በነፃ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ እና ለታካሚዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መድኃኒቶች ግዥ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO፣ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶች ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅበታል። በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ የሚፈልጉ ገንዘቡን በኮሌጁ ፋይናንስ ክፍል GOV1000257812956 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በመክፈቻው ስዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የጨረታ ማስከበሪያ በማቅረብ ምትክ ተቋማቱን ከአደራጀው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
    1. 60 ሰውና ከዚያ በላይ የሚጭን የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።
    2. ለታካሚዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መድኃኒቶች ግዥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡- ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን ካላንደር የሚዘጋው እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

  1. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበትን ቅፅ ሞልተውና ፈርመው ከመወዳደሪያ ሠነዳቸው ጋር ለመመለስ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
  2. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  3. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  4. ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 058320-9320 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

 

Save Tender