በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ ቦሌ ለጤና ጣቢያ የ2017 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ CBC (complete blood count) ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ ቦሌ ጤና ጣቢያ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ ቦሌ ለጤና ጣቢያ የ2017 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ CBC (complete blood count) ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ TIN NO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን የአየር ላይ ቆይታ በኋላ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ:- 25,000 /ሀያ አምስት ሺ ብር / ሲፒኦ (CPO) በጉመር ወረዳ ቦሌ ጤና ጣቢያ ስም በማሰራት ኦሪጅናል ዶክመንት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ:-
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጉመር ወረዳ ቦሌ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 22 በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 22 መውሰድ ይቻላል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ከላይ በተራ ቁጥር 1 ፣ 2 እና 3 ላይ የተገለፁት ዶክመንቶች/ መረጃዎች ዋናው እና ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒው በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይዛወራል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0933 70 81 21/0920 81 74 49
በማዕ/ኢት/ክ/ በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ ቦሌ ጤና ጣቢያ ጽ/ቤት አረቅጥ
