የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ለፋሚገሽን ሺት (Famigation sheet) ሻራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው ከአቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የተዘረዘሩት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
Busa Gonofa Oromia (የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ)
የፋሚገሽን ቪት (Famigtion sheet)
ሻራ ግዥ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BGO 04/2017
የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ለፋሚገሽን ሺት (Famigation sheet) ሻራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው ከአቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የተዘረዘሩት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡-
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-
- ለዘመኑ የታደሰ የሥራ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የተሰጠ የጽሁፍ ማስረጃ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የተሰጠ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማስረጃ
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 20 መውሰድ አለባቸው፡፡
- ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ብቻ የጨረታ ሰነዶቹን ዋናና ኮፒውን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 20 ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ አዳራሽ ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒአ /CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ አብሮ ይቀርባል
- ጨረታውን አሸንፈው ውሉን ሲፈርሙ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የሥራ አፈጻጸም ዋስትና CPO ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ በቅድሚያ ያሲይዛሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ መወዳደሪያ ሃሳብ/ዋጋ በመሙላት ዋና እና ቅጂውን ለየብቻ በኤንቨሎፕ አሽገው የድርጅታቸውን ሙሉ አድራሻ በመግለጽ ማቅረብ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር-251114709028 በመደወል መጠየቅ ይቻላሉ።
አድራሻ፡- ሳሪስ አዲስ ጎማ /ሆራይዘን/ ፋብሪካ ፊት ለፊት
የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ
