በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ገባ/ዲዲሳ ዲስትሪክት ላይ በንፋስ የወደቀ የፈረንጅ ጥድ ግንዲላ እንዲሁም ጂማ ቅ/ጽ/ቤት ሲግሞ ሰጠማ ዲስትሪክት ላይ በንፋስ የወደቀ የፈረንጅ ጥድ እና የ“Grevillea robusta” ድብልቅ ግንዲላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Oromia Forest and Wildlife Enterprise (OFWE) (የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት)
የደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OFWE/GU-13/2017
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት ገባ/ዲዲሳ ዲስትሪክት ላይ በንፋስ የወደቀ የፈረንጅ ጥድ ግንዲላ እንዲሁም ጂማ ቅ/ጽ/ቤት ሲግሞ ሰጠማ ዲስትሪክት ላይ በንፋስ የወደቀ የፈረንጅ ጥድ እና የ“Grevillea robusta” ድብልቅ ግንዲላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጀሎ ሙክታር ሃደስ ዲስትሪክት፤ ጂማ ቅ/ጽ/ቤት በለጠ ጌራ እና በቢያ ፎላ ዲስትሪክቶች ላይ የቁም የፈረንጅ ጥድ ግንዲላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
- የግንዲላ እና የእንጨት መሰንጠቂያ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢና “TN number” ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል ቀበና ሼል/ ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በወጣበት ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ጅማ ከተማ፤ ኢሉ አባ ቦራ ቅ/ጽ/ቤት መቱ ከተማ፤ ሀረርጌ ቅ/ጽ/ቤት ጭሮ ከተማ በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲቆይ ለሁለተኛ ጊዜ የወጣው ደግሞ ለ10 ተከታታይ ቀናት ይቆያል።
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ትክክለኛው ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች ፤ በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO)ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 124 0249 በመደወል ማጠየቅ ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
