Tender Detail

Tender Details


የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ለሚያስገነባቸው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች አቅርቦትና ስራ ማሽነሪና ተሽከርካሪ ግዥ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።


 

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ለሚያስገነባቸው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች አቅርቦትና ስራ ማሽነሪና ተሽከርካሪ ግዥ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።

  • ምድብ 1 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለደ/ማርቆስ አዲሱ መናኸሪያ ግንባታ ጀኔሬተር አቅርቦትና ገጠማ
  • ምድብ 2 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፕሮጀክት ዋተር ፕሩፍ አቅርቦትና ስራ
  • ምድብ 3 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለጂ+1ዐ ህንፃ ግንባታ አገልግሎት የሚውል ዋተር ፕሩፍ አቅርቦትና ስራ
  • ምድብ 4 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለጂ+10 ህንፃ ግንባታ አገልግሎት የሚውል ስካይ ላይት አቅርቦትና ስራ
  • ምድብ 5 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለጂ+10 ህንፃ ግንባታ አገልግሎት የሚውል የብረት በር አቅርቦትና ስራ
  • ምድብ 6 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለጂ+10 ህንፃ ግንባታ አገልግሎት የሚውል ቶሌት ፓርቲሽን አቅርቦትና ስራ
  • ምድብ 7 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለጂ+10 ደ/ማ አልማ ህንፃ ግንባታ ስቶን ክላዲንግ አቅርቦትና ገጠማ
  • ምድብ 8 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለጂ+10 ደ/ማርቆስ አልማ ህንፃ ግንባታ አልሙኒዬም መስኮት አቅርቦት እና ስራ
  • ምድብ 9 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለጂ+10 ደ/ማርቆስ አልማ ህንፃ ግንባታ ከርቴን ወል አቅርቦት እና ስራ
  • ምድብ 10 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውል አውቶቢስ አቅርቦት
  • ምድብ 11 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውል ፎርክ ሊፍት አቅርቦት
  • ምድብ 12 የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውል ዋተር ትራክ አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስቀረብና ማሰራት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ሰነድ ያንዱን ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት አለባችሁ።
  2. ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ የጨረታ መከፈቻ ቀኑ በበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል። ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመከፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  3. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የገበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመቅረብ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  5. በየምድባቸው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  6. አሸናፊው ድርጅት ከምድብ 1 እስከ ምድብ 9 ያሉ ዕቃዎችን በየፕሮጀክቱ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ገጥሞ ማስረከብ ይኖርበታል።
  7. ከምድብ 1 እስከ 9 ያሉት ዕቃ አቅርቦት ወይም አቅርቦትና ስራዎች ማቴሪያል አቅርበው ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት ካታሎግ ካምፓኒ ፕሮፋይል ወይም ማቴሪያል በማቅረብ ቴስት አፕሩቫል ማሰራት ይኖርበትም።
  8. ምድብ 8 እና 9 አሸናፊው ድርጅት በተቀመጠው ድሮይንግ መሰረት ሰርቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠ/ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው
  10. ከምድብ 10 እስከ 12 ያሉ ማሽነሪ እና ተሽከርካሪዎች በተቀመጠው ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለበት።
  11. አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው እቃዎች እና ስራ በባለሙያ ወይም ቴስት ተረጋግጦ ማለፍ አለበት።
  12. አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል።
  13. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ የመድን ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
  14. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ይዘው ወደ ስራ መግባት አለባቸው።
  15. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 20 51 44 07 ደውስው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በምስ/ጎጃም ዞን በደ/ማ ከተማ/አስ መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት

 

Save Tender