የሐሴት ጅምላ ንግድ ቢዝነስ አከሲዮን ማህበር ላቀደው የግንባታ ስራ ገዝቶ በዋና መስሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጠው የሚገኙትን የግንባታ ግብዓቶች፣ ባጋጠመው የገንዘብ እጥረት ግንባታውን ማካሄድ ባለመቻሉ ምክንያት፣ አቅም እስከሚፈጠር ድረስ የግንባታ ቁሳቁሶቹን ከብልሽት ለመከላከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የሐሴት ጅምላ ንግድ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የሐሴት ጅምላ ንግድ ቢዝነስ አከሲዮን ማህበር ላቀደው የግንባታ ስራ ገዝቶ በዋና መስሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጠው የሚገኙትን የግንባታ ግብዓቶች፣ ባጋጠመው የገንዘብ እጥረት ግንባታውን ማካሄድ ባለመቻሉ ምክንያት፣ አቅም እስከሚፈጠር ድረስ የግንባታ ቁሳቁሶቹን ከብልሽት ለመከላከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግንባታ ግብዓቶች በመነሻ ዋጋቸው መሰረት በግልጽ ጨረታ ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ እንዲወዳደር እንጋብዛለን።
ለሽያጭ የቀረቡ የግንባታ ግብዓቶች ዝርዝር:
- የቤት ክዳን ቆርቆሮ:
- ዓይነት: ባለ ፈረስ ምልክት ፣ 2ኛው ደረጃ 35 ጌጅ
- ብዛት፡ 100 በቁጥር
- የአንዱ መነሻ ዋጋ፡ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- የአገር ውስጥ ምርት የአርማታ ብረቶች:
|
ተ/ቁ |
ዓይነት |
መጠን ቤርጋ |
የአንዱ መነሻ መሸጫ ዋጋ |
|
1 |
ባለ 8 ሚ/ሜ |
300 |
790.53 |
|
2 |
ባለ 10 ሚ/ሜ |
350 |
1251.62 |
|
3 |
ባለ 12 ሚ/ሜ |
300 |
1782.39 |
|
4 |
ባለ 14 ሚ/ሜ |
30 |
2443.71 |
|
5 |
ባለ 16 ሚ/ሜ |
150 |
3141.58 |
|
6 |
ባለ 20 ሚ/ሜ |
150 |
4924.94 |
የጨረታው ሁኔታዎች፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል፣ ከሐሴት ጅምላ ንግድ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ንግድ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን የግንባታ ግብዓቶች ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተከርስቲያን ገባ ብሎ ከሐሴት ጅምላ ንግድ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ተመላሽ የሚደረግ 20% የባንክ ማረጋጋጫ ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም ለተሸነፉት ወዲያውኑ ተመላሽ ሲደረግ ላሸነፉት በሚገዙበት ዋጋ ላይ ታሳቢ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና የድርጅቱ የሽያጭ ኮሚቴዎች በተገኙበት ግንቦት 23/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: +251 114 403103/0930000129 ወይም በአካል አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 07 ገብርኤል ቤተከርስቲያን ጀርባ በመቅረብ ማየት/ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
ሐሴት ጅምላ ንግድ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር
