በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ስፖርት ፅ/ቤት 1ኛ የወጣት ማዕከል ግንባታ በዘመሮ ከተማ ውስጥ በአልማ በጀት ደረጃ BC/GC 7 እና በላይ ያላቸውን የንግድ ድርጅቶች አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
የግንባታ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ስፖርት ፅ/ቤት 1ኛ የወጣት ማዕከል ግንባታ በዘመሮ ከተማ ውስጥ በአልማ በጀት ደረጃ BC/GC 7 እና በላይ ያላቸውን የንግድ ድርጅቶች አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል። በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ፣ አግባብነት ያለው ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) እና የቫት ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ ማስረጃ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመግዛት የሚሰሩበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ መሰረት በመሙላት አንድ አርጂናል በማሸግ በመ/ቀ/ገ/ወ/ገ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ
- ተጫራች የግንባታውን አጠቃላይ አቅርቦት ወጪ እና ሙያውን ችሎ የሚሰራበትን ዋጋ መሙላት አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሞሉትን ዋጋ 2% ከነቫቱ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ግንባታውን ለመስራት ሙሉ በሙሉ የማቴሪያሉን እና የእጅ ዋጋ መሙላት አለባቸው።
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 21 ተከታታይ ቀን ሲሆን በ22ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል 22ኛው ቀን የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ዝርዝር ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ፣ በፍሉድ የተሰረዘ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ የሆነ ሰነድ የተከለከለና ከጨረታ የሚያሰርዝ ነው፡፡
- ለጨረታ የሚያስፈልገውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ያላቀረቡ ተጫራቾች በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት ከጨረታ ወጪ ይደረጋሉ።
- የተጫራቾች ፖስታ በሰም ባለመታሸጉ ከጨረታ አያሰርዝም።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ መሆን አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ 25% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል ያልፈጸሙ እንደሆነ ግዥ ፈጻሚው አካል የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው፡፡
ስልክ ቁጥር 0913247806 /0921747797
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
