በአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ በኮምቦልቻ ሪጂአፖሊታንት ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ እና ህንፃ መሳሪያ ወይም ለፈርኒቸር የሚሆኑ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ በኮምቦልቻ ሪጂአፖሊታንት ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ እና ህንፃ መሳሪያ ወይም ለፈርኒቸር የሚሆኑ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስከ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፍያ መለያ ቁጥርና የቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 200 ብር በአንድ ሎት በመክፈል ከኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 014 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን በሰም በታሸገ ፖስታ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ ቀጥሎ በሚውለው በ16ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- በቀረበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 014 መጥተው ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከብር 20,000 በላይ ለሚፈፀመው ግዥዎች መ/ቤቱ 7.5 ቫት ህጋዊ ደረሰኝ የሚሰጥ መሆኑን እያሳወቅን
- አሸናፊ ድርጅት እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት ለኮሌጁ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
